1
መጽሐፈ መክብብ 4:9-10
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ያነሣዋልና፥ አንድ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 4:12
አንዱም ሌላውን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፤ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።
3
መጽሐፈ መክብብ 4:11
ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል?
4
መጽሐፈ መክብብ 4:6
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል።
5
መጽሐፈ መክብብ 4:4
እኔ ድካምን ሁሉና የብልሃት ሥራውን ተመለከትሁ፥ ለሰውም በባልንጀራው ዘንድ ቅንአትን እንዲያስነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
6
መጽሐፈ መክብብ 4:13
ድሃና ጠቢብ ብላቴና ከእንግዲህ ወዲህ ተግሣጽን መቀበል ከማያውቅ ከሰነፍ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች