1
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:11
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:12
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ የሥልጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኀይልን ለመስጠት ዓለምን ሁሉ በእጅህ የያዝህ ነህ።
3
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:14
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
4
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:13
አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ፥ እንገዛልሃለን፤ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።
5
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:10
ንጉሡ ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ቡሩክ ነህ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች