ጌታም መልሶ ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ይህ በልብህ ነበረና፥ ባለጸግነትንና ሀብትን ክብርንና የጠላቶችህን ነፍስ ረጅምም ዕድሜን አልጠየቅህምና፥ ነገር ግን ባነገሥሁህ በሕዝቤ ላይ ለመፍረድ እንድትችል ጥበብንና እውቀትን ለራስህ ጠይቀሃልና፥ ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”