1
ትንቢተ ሚክያስ 4:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አሕዛብ ሁሉ እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸውን ያመልካሉ፤ እኛ ግን አምላካችንን እግዚአብሔርን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም እናመልካለን።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ሚክያስ 4:2
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፥ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ፥ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
3
ትንቢተ ሚክያስ 4:1
የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ፥ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተሠራበት ተራራ ከሌሎች ተራራዎች ሁሉ በልጦ ይታያል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ እጅግ ከፍ ይላል፤ የብዙ መንግሥታት ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
4
ትንቢተ ሚክያስ 4:3
እርሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በቅርብና በሩቅ ባሉ ታላላቅ መንግሥታት መካከል ያለውን አለመግባባት ያስወግዳል፤ ስለ ሆነም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያ በኋላም የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች