1
መጽሐፈ መክብብ 7:9
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ቊጣ የሰነፎች ቂም በቀል መወጫ ስለ ሆነ የቊጡነት ስሜትህን ተቈጣጠር።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 7:14
ጊዜው መልካም ሲሆን ደስ ይበልህ፤ ጊዜውም ክፉ ሲሆን አስተውል፤ ይህንንም ያንንም ያደረገ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ሰው ማንኛውንም የወደፊት ሁናቴውን ሊያውቅ አይችልም።
3
መጽሐፈ መክብብ 7:8
ማናቸውም ነገር ከመጀመሪያው ይልቅ ፍጻሜው የተሻለ ነው፤ በትዕቢት ከሚናገር ሰው ይልቅ ትዕግሥተኛ ሰው ይሻላል።
4
መጽሐፈ መክብብ 7:20
ምንም ስሕተት ሳይፈጽም ሁልጊዜ መልካም ነገርን የሚሠራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም።
5
መጽሐፈ መክብብ 7:12
ጥበብ እንደ ገንዘብ ከለላ ነች፤ ከዚያም በላይ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትጠብቃለች።
6
መጽሐፈ መክብብ 7:1
ዋጋው ውድ ከሆነ ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል።
7
መጽሐፈ መክብብ 7:5
የሞኞችን ዘፈን ከመስማት የጥበበኞችን ተግሣጽ መስማት ይሻላል።
8
መጽሐፈ መክብብ 7:2
ሞት በሰው ሁሉ ላይ የሚደርስ መሆኑን እንዲገነዘቡ ስለሚያደርግ ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ለቅሶ ቤት መሄድ ይመረጣል።
9
መጽሐፈ መክብብ 7:4
ሁልጊዜ ስለ አስደሳች ነገር ብቻ የሚያስብ ሰው ሞኝ ነው፤ ብልኅ ግን የሞትንም ነገር ያስባል።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች