1
መጽሐፈ መክብብ 3:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
በዚህ ዓለም ለሚፈጸም ለማናቸውም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የወሰነለት ዘመንና ጊዜ አለው፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 3:2-3
ስለዚህም እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፥ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀል ጊዜ አለው። ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለመገንባት ጊዜ አለው፤ ለማፍረስም ጊዜ አለው።
3
መጽሐፈ መክብብ 3:4-5
ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለመጨፈርም ጊዜ አለው። ድንጋይ ለመበተን ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው።
4
መጽሐፈ መክብብ 3:7-8
ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለንግግርም ጊዜ አለው። ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።
5
መጽሐፈ መክብብ 3:6
ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ የጠፋውን ላለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፤ ለመጣልም ጊዜ አለው።
6
መጽሐፈ መክብብ 3:14
እግዚአብሔር የሠራው ነገር ሁሉ ዘለዓለማዊነት እንዳለው ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ የሚጨመርበት ወይም ከእርሱ የሚቀነስ ነገር የለም፤ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ሰዎች እርሱን እንዲፈሩት ነው።
7
መጽሐፈ መክብብ 3:17
እኔም “ሁሉ ነገር የሚፈጸምበት ጊዜ ስላለው እግዚአብሔር በዐመፀኞችም ሆነ በቅኖች ላይ ይፈርዳል” ብዬ አሰብኩ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች