1
ዘዳግም 18:10-11
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ጠንቋይ ወይም በድግምት የሚጠነቍል፣ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘዳግም 18:12
እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።
3
ዘዳግም 18:22
ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።
4
ዘዳግም 18:13
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ነውር አልባ ሁን።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች