← እቅዶች
ከ ፊልጵስዩስ 2:8ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች

ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴር
3 ቀናት
የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡

የዕዝራ መጽሐፍ የወንጌል ዕይታ
3 ቀናት
እግዚአብሔር የገባልህን የተስፋ ቃል እንዴት እንደሚፈፅመው ትገረም ይሆን? ፍሬያማ ኑሮስ ለመኖር ተስፋ ታደርጋለህ? የዕዝራ መጽሐፍ የሚዳስሰው እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግና ለማደስ የተስፋ ቃሉን መፈፀሙን ሲሆን ከዚህም የተነሳ የኖሩትን ፍሬያማ ኑሮ ያሳያል፡፡ በዕዝራ አስደማሚ ታሪክ ውስጥ የሚታየው አግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የገባው ትልቁ የተስፋ ፍፃሜ የሆነውና ብቸኛው የፍሬያማነት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ነው፡፡