ኦሪት ዘፀአት 10:21-23
ኦሪት ዘፀአት 10:21-23 አማ2000
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለማውም የሚዳሰስ ነው” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤ ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመኝታው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበራቸው።