1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ “ተፈጸመ” አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
對照
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:30
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ “ተጠማሁ” አለ።
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:28
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ “አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፦ “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህ የሆነ፦ “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው መጽሐፍ፦ “የወጉትን ያዩታል” ይላል።
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ።
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:17
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤
探尋 የዮሐንስ ወንጌል 19:2
首頁
聖經
計畫
視訊