1
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ።
對照
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
2
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ። አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
3
ኦሪት ዘፀአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:12
4
ኦሪት ዘፀአት 20:8
“የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:8
5
ኦሪት ዘፀአት 20:7
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:7
6
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ አህያህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርስዋ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
7
ኦሪት ዘፀአት 20:17
“የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።”
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:17
8
ኦሪት ዘፀአት 20:16
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:16
9
ኦሪት ዘፀአት 20:14
“አታመንዝር።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:14
10
ኦሪት ዘፀአት 20:13
“አትግደል።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:13
11
ኦሪት ዘፀአት 20:15
“አትስረቅ።
探尋 ኦሪት ዘፀአት 20:15
首頁
聖經
計畫
視訊