ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች መግቢያ

መግቢያ
ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው፥ መቄዶንያ በሚባለው የሮም ግዛት ስር በፊልጵስዩስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ነው፤ ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮጳ ምድር ያቋቋማት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት፤ መልእክቱ የተጻፈው ጳውሎስ እስር ቤት በነበረበት፥ ከሌሎች ክርስቲያን አገልጋዮች ተቃውሞ በደረሰበት ጊዜና በፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን በተነሣው የሐሰት ትምህርት ምክንያት ልቡ በኀዘን በተሰበረበት ወቅት ነው። ይሁን እንጂ ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለው እምነት እጅግ የጠለቀ በመሆኑ በዚህ መልእክት ጐልቶ የሚታየው ደስታና ሙሉ መተማመን ነው።
ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈበት ተቀዳሚ ምክንያት በችግሩ ጊዜ እርሱን ለመርዳት ስጦታ ልከውለት ስለ ነበር የፊልጵስዩስን ምእመናን ለማመስገን ነው፤ በእርሱም ሆነ በእነርሱ ላይ ልዩ ልዩ ችግሮች የደረሱ ቢሆኑም እንኳ ድፍረትና ሙሉ መተማመን እንዲኖራቸው በዚህ አጋጣሚ ያበረታታቸዋል። ትዕቢትንና ትምክሕትን አስወግደው በኢየሱስ ክርስቶስ ትሕትና እንዲሞሉ በጥብቅ ያሳስባቸዋል፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመንፈስ አንድ በመሆን ያገኙት ሕይወት ከእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ የመነጨና በእምነት የተቀበሉት እንጂ ሕግን በመፈጸም የተገኘ አለመሆኑን ያስታውሳቸዋል፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመተባበር ለሚኖሩ ሁሉ እግዚአብሔር ስለሚሰጣቸው ሰላምና ደስታም ይጽፍላቸዋል።
ይህ መልእክት የሚታወቀው ደስታን፥ መተማመንን፥ ኅብረትንና በክርስትና እምነትና ሕይወት መጽናትን አጒልቶ በማሳየቱ ነው፤ በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ታላቅ ፍቅር ይገልጣል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-11)
ጳውሎስ የነበረበት ግላዊ ሁኔታ (1፥12-26)
የክርስትና ሕይወት ምሳሌ (1፥27—2፥18)
የጢሞቴዎስና የኤጳፍሮዲጡስ አገልግሎት (2፥19-30)
ከእምነት ተቃዋሚዎች ማስጠንቀቂያ (3፥1—4፥9)
ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ያቀረበው ምስጋናና ምክር (4፥10-20)
ማጠቃለያ (4፥21-23)
ምዕራፍ

醒目顯示

分享

複製

None

想在你所有裝置上儲存你的醒目顯示?註冊帳戶或登入