1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
對照
የማርቆስ ወንጌል 13:13 探索
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።
የማርቆስ ወንጌል 13:33 探索
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
የማርቆስ ወንጌል 13:11 探索
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
የማርቆስ ወንጌል 13:31 探索
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።
የማርቆስ ወንጌል 13:32 探索
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:7 探索
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37 探索
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
የማርቆስ ወንጌል 13:8 探索
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።
የማርቆስ ወንጌል 13:10 探索
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:6 探索
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:9 探索
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:22 探索
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25 探索
主頁
聖經
計劃
影片