1
የሉቃስ ወንጌል 6:38
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስጡ ይሰጣችኋልም፤ በመልካምም መስፈሪያ የተጠቀጠቀና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና።”
對照
የሉቃስ ወንጌል 6:38 探索
2
የሉቃስ ወንጌል 6:45
መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።
የሉቃስ ወንጌል 6:45 探索
3
የሉቃስ ወንጌል 6:35
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።
የሉቃስ ወንጌል 6:35 探索
4
የሉቃስ ወንጌል 6:36
አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።
የሉቃስ ወንጌል 6:36 探索
5
የሉቃስ ወንጌል 6:37
“አትፍረዱ እንዳይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ እንዳትኰነኑም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ፤
የሉቃስ ወንጌል 6:37 探索
6
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28
“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28 探索
7
የሉቃስ ወንጌል 6:31
እንዲሁም ሰዎች ለእናንተ እንዲያደርጉላችሁ የምትወድዱትን ነገር እናንተ ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:31 探索
8
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30
ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጉንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን እንኳ አትከልክለው። ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህንም የሚወስድብህን ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30 探索
9
የሉቃስ ወንጌል 6:43
መልካም ዛፍ የተበላሸ ፍሬ አያፈራምና፤ እንዲሁም የተበላሸ ዛፍ መልካም ፍሬ አያፈራም።
የሉቃስ ወንጌል 6:43 探索
10
የሉቃስ ወንጌል 6:44
ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ከአጣጥ ቁጥቋጦም ወይን አይቈርጡም።
የሉቃስ ወንጌል 6:44 探索
主頁
聖經
計劃
影片