1
የሐዋርያት ሥራ 26:17-18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከእስራኤል ሕዝብና ወደ እነርሱ ከምልክህ አሕዛብ እጅ አድንሃለሁ። ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
對照
የሐዋርያት ሥራ 26:17-18 探索
2
የሐዋርያት ሥራ 26:16
አሁን ግን ተነሥና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥኩልህ አሁን እኔን ባየህበትና ወደፊትም እኔ ለአንተ በምገለጥበት ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆነኝ ልሾምህ ፈልጌ ነው።
የሐዋርያት ሥራ 26:16 探索
3
የሐዋርያት ሥራ 26:15
እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።
የሐዋርያት ሥራ 26:15 探索
4
የሐዋርያት ሥራ 26:28
አግሪጳም ጳውሎስን፥ “አንተ በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስቲያን ልታደርገኝ ነው እኮ” አለው።
የሐዋርያት ሥራ 26:28 探索
主頁
聖經
計劃
影片