1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች መግቢያ

መግቢያ
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈላቸው የመጀመሪያው መልእክት በቆሮንቶስ ባቋቋመው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ ክርስትና ሕይወትና እምነት ተነሥቶ ለነበረው ችግር መፍትሔ ለማስገኘት በማሰብ ነው። በዚያን ጊዜ ቆሮንቶስ ዓለም ዐቀፋዊት የሆነች የግሪክ ከተማ ከመሆንዋም በላይ አካይያ ለተባለ የሮም ግዛት ዋና ከተማ ነበረች። ይህች ከተማ ታላቅ በሆነ የንግድ እንቅስቃሴ፥ በደረጀ ባህል፥ በመስፋፋት ላይ በነበረ ምግባረ ብልሹነትና በሃይማኖቶች ብዛት የታወቀች ነበረች።
ሐዋርያው በተለይ ያተኰረው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ስለ ነበረው መከፋፈል፥ ስለ ምግባረ ብልሹነትን፥ ስለ ዝሙትና ስለ ጋብቻ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ስለ ትንሣኤ ነበር፤ እንዲሁም ሐዋርያው የምሥራቹን ቃል በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ በማተኰር በጥንቃቄ ያቀርባል።
“ፍቅር” እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጣቸው ስጦታዎች የበለጠ መሆኑን የሚገልጠው ዐሥራ ሦስተኛው ምዕራፍ ከዚህ መጽሐፍ እጅግ ታዋቂ የሆነው ክፍል እንደሆነ ይገመታል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-9)
በክርስቲያኖች መካከል የተነሣ መከፋፈል (1፥10—4፥21)
ምግባረ ብልሹነትና የቤተሰብ ሕይወት (5፥1—7፥40)
ክርስቲያኖችና የክርስቲያን እምነት ያልተቀበሉ (8፥1—11፥1)
የቤተ ክርስቲያን ሕይወትና የአምልኮ ሥርዓት (11፥2—14፥40)
የክርስቶስና የአማኞች ትንሣኤ (15፥1-58)
በይሁዳ ላሉ ለተቸገሩ ክርስቲያኖች ርዳታ (16፥1-4)
ማጠቃለያ (16፥5-24)
ምዕራፍ

高亮显示

分享

复制

None

想要在所有设备上保存你的高亮显示吗? 注册或登录