የማርቆስ ወንጌል መግቢያ

መግቢያ
የማርቆስ ወንጌል “ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የምሥራች ቃል መጀመሪያ ነው” በማለት ይነሣል፤ በዚህ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ የሥራና የሥልጣን ሰው በመሆን ቀርቦአል፤ ሥልጣኑም በትምህርቱ፥ በአጋንንት ላይ ባለው ኀይልና የሰውን ኃጢአት ይቅር በማለቱ ታይቶአል። ኢየሱስ “ሰዎችን ከኃጢአት ባርነት ነጻ በማውጣት ሕይወቴን ቤዛ አድርጌ ለመስጠት የመጣሁ የሰው ልጅ ነኝ” በማለት ራሱ ተናግሮአል።
ማርቆስ የኢየሱስን ታሪክ ያቀረበው፥ ቀጥተኛና ኀይልን በተሞላ መንገድ ሲሆን ያተኰረውም በኢየሱስ ቃልና ትምህርት ላይ ሳይሆን ባከናወናቸው ድንቅ ሥራዎች ላይ ነበር። ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ፥ ስለ ኢየሱስ ጥምቀትና ፈተና አጠር ያለ መግቢያ ከሰጠ በኋላ ጸሐፊው ስለ ኢየሱስ የማስተማርና የመፈወስ አገልግሎት ይተነትናል። ከጊዜ በኋላ የኢየሱስ ተከታዮች ኢየሱስን በበለጠ ሁኔታ እያወቁ በሄዱ መጠን የኢየሱስ ተቃዋሚዎችም ይበልጡን እየጠሉት ሄዱ። የመጨረሻዎቹ ምዕራፎች በኢየሱስ ሕይወት በመጨረሻው ሳምንት ውስጥ ስለ ተፈጸሙት ድርጊቶች፥ በተለይም ስለ ስቅለቱና ስለ ትንሣኤው የሚተርኩ ናቸው።
በወንጌሉ መጨረሻ ላይ በቅንፍ የተመለከቱት ሁለት ክፍሎች በአንዳንድ ቅጂዎች ብቻ የሚገኙ ናቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የወንጌሉ መጀመሪያ 1፥1-13
ኢየሱስ አገልግሎቱን በገሊላ መጀመሩ 1፥14—9፥50
በኢየሩሳሌም ማገልገሉ 10፥1-52
በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ የመጨረሻ ሳምንት 11፥1—15፥47
የጌታ ትንሣኤ 16፥1-8
ከሞት የተነሣው ጌታ መገለጥና ዕርገቱ 16፥9-20

高亮显示

分享

复制

None

想要在所有设备上保存你的高亮显示吗? 注册或登录