ኦሪት ዘሌዋውያን መግቢያ

መግቢያ
ኦሪት ዘሌዋውያን የሚያትተው በጥንታዊት እስራኤል ስለ ነበሩት የአምልኮ ደንቦችና ስለ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው፤ እንዲሁም እነዚህን ሥርዓቶች በተግባር የመተርጐም ኀላፊነት ስለ ነበራቸው ካህናት ይገልጣል።
የመጽሐፉ ማእከላዊ ሐሳብ ስለ እግዚአብሔር ቅድስና የሚናገር ነው፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሕዝብ ከዚሁ ቅዱስ ከሆነው ከእስራኤል አምላክ ጋር የቅርብ ግንኙነት ይኖራቸው ዘንድ፥ በእንዴት ያለ ሁኔታ ማምለክ እንደሚገባቸው ይዘረዝራል።
ከመጽሐፉ ውስጥ በጣም የታወቀው ትእዛዝ ኢየሱስ ሁለተኛው ታላቅ ትእዛዝ ብሎ የሠየመውና በም. 19 ቊ. 18 ላይ የሚገኘው ነው፤ እርሱም “ሰውን ሁሉ እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” የሚለው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሀ. የመባና የመሥዋዕት ሕግ 1፥1—7፥38
ለ. የአሮንና የልጆቹ የክህነት ሹመት 8፥1—10፥20
ሐ. ንጹሕ የሆነና ያልሆነ ነገር፥ እንዲሁም የመንጻት ሥርዓት 11፥1—15፥33
መ. የኃጢአት ስርየት ቀን 16፥1-34
ሠ. የቅድስና ሕይወትና የአምልኮ ሕግ 17፥1—27፥34

高亮显示

分享

复制

None

想要在所有设备上保存你的高亮显示吗? 注册或登录