1
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
对照
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎታችሁ ነው።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
እርስ በእርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተከባበሩ፤
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
ፍቅር እውነተኛ ይሁን፤ ክፉውን ነገር ተጸየፉ፥ መልካም የሆነው ነገር አጥብቃችሁ ያዙ፤
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ ነገር ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፤ ነገር ግን የተናቁትን ቅረቡ። በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
ነገር ግን ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማው አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉን፥ የሰውነት ክፍሎቹም ሥራ አንድ እንዳልሆነ ሁሉ፥ እንዲሁም ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በእርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው የሰውነት ክፍሎች ነን።
探索 ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
主页
圣经
计划
视频