YouVersion 标志
圣经计划视频
获取软件
选择语言
搜索图标

ኦሪት ዘፍጥረት 6 的热门经文

1

ኦሪት ዘፍጥረት 6:6

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ስለዚህ ሰዎችን በመፍጠሩና በምድር ላይ እንዲኖሩ በማድረጉ አዘነ፤ እጅግም ተጸጸተ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:6

2

ኦሪት ዘፍጥረት 6:5

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ዐመፀኞች እንደ ሆኑና ሐሳባቸውም ዘወትር ክፋት ብቻ እንደ ሆነ ተመለከተ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:5

3

ኦሪት ዘፍጥረት 6:8

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ይሁን እንጂ ኖኅ የተባለው ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝቶ ነበር።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:8

4

ኦሪት ዘፍጥረት 6:9

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ኖኅ በዘመኑ ምንም በደል የማይሠራና የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተል ደግ ሰው ነበር፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:9

5

ኦሪት ዘፍጥረት 6:7

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር “እነርሱን በመፍጠሬ አዝኛለሁ፤ ስለዚህ እነዚህን የፈጠርኳቸውን ሰዎች፥ እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና ወፎችንም ጭምር ከምድር ላይ አጠፋለሁ” አለ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:7

6

ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-4

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

የሰው ዘር በምድር ላይ እየበዛ በሄደ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱ፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች የእነዚህን የሰውን ሴቶች ልጆች ውበት ተመለከቱ፤ ከመካከላቸውም የሚወዱአቸውን እየመረጡ ወሰዱ። እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ። በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-4

7

ኦሪት ዘፍጥረት 6:22

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:22

8

ኦሪት ዘፍጥረት 6:13

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:13

9

ኦሪት ዘፍጥረት 6:14

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ በውስጡም ብዙ ክፍሎች እንዲኖሩት አድርግ፤ መርከቡን ከውስጥና ከውጪ በቅጥራን ለቅልቀው።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:14

10

ኦሪት ዘፍጥረት 6:12

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

እግዚአብሔር ዓለምን ተመለከተ፤ የተበላሸች እንደ ሆነችና በውስጧም ያሉት ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ።

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:12

11

ኦሪት ዘፍጥረት 6:19

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አማ05

“ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲጠበቁ ሥጋ ከለበሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ከየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየወሰድህ ወደ መርከቡ አስገባ፤

对照

探索 ኦሪት ዘፍጥረት 6:19

上一章
下一章
YouVersion

我们要鼓励、挑战你每天亲近上帝。

事工

关于我们

就职机会

义工

博客

新闻区

有用链接

帮助

捐赠

圣经译本

音频圣经

译本语言

今日经文


此数字事工属于

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

隐私政策使用条款
漏洞披露方案
FacebookTwitterInstagramYouTubePinterest

主页

圣经

计划

视频