1
ወደ ሮም ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮም ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮም ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮም ሰዎች 8:1
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮም ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮም ሰዎች 8:37
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮም ሰዎች 8:18
ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮም ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮም ሰዎች 8:27
ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮም ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮም ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮም ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮም ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮም ሰዎች 8:19
የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮም ሰዎች 8:22
ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
Ṣàwárí ወደ ሮም ሰዎች 8:22
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò