1
የሉቃስ ወንጌል 5:4
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:4
2
የሉቃስ ወንጌል 5:5-6
ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:5-6
3
የሉቃስ ወንጌል 5:16
ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:16
4
የሉቃስ ወንጌል 5:32
ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:32
5
የሉቃስ ወንጌል 5:8
ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:8
6
የሉቃስ ወንጌል 5:31
ኢየሱስም መልሶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:31
7
የሉቃስ ወንጌል 5:11
ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:11
8
የሉቃስ ወንጌል 5:12-13
ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የሞላበት ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም አይቶ በፊቱ ወደቀና፦ ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:12-13
9
የሉቃስ ወንጌል 5:15
ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 5:15
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò