1
የሉቃስ ወንጌል 17:19
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:19
2
የሉቃስ ወንጌል 17:4
በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:4
3
የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
4
የሉቃስ ወንጌል 17:3
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:3
5
የሉቃስ ወንጌል 17:17
ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ?
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:17
6
የሉቃስ ወንጌል 17:6
ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:6
7
የሉቃስ ወንጌል 17:33
ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:33
8
የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤ ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
9
የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò