1
የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ከዐመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
2
የማቴዎስ ወንጌል 24:14
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 24:6
ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:6
4
የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
5
የማቴዎስ ወንጌል 24:35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:35
6
የማቴዎስ ወንጌል 24:5
ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:5
7
የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
8
የማቴዎስ ወንጌል 24:4
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 24:44
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:44
10
የማቴዎስ ወንጌል 24:42
ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:42
11
የማቴዎስ ወንጌል 24:36
“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:36
12
የማቴዎስ ወንጌል 24:24
ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
Ṣàwárí የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò