1
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ጌታችን ኢየሱስም አላት፥ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞትም ይነሣል። ሕያው የሆነ የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም፤ ይህንስ ታምኛለሽን?”
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
2
የዮሐንስ ወንጌል 11:40
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ብታምናስ የእግዚአብሔርን ክብር ታያለሽ አላልሁሽም ነበርን?” አላት።
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:40
3
የዮሐንስ ወንጌል 11:35
ጌታችን ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:35
4
የዮሐንስ ወንጌል 11:4
ጌታችን ኢየሱስም ሰምቶ እንዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም።”
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:4
5
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
ይህንም ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸና፥ “አልዓዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ። ሞቶ የነበረውም እንደ ተገነዘ፥ እጁንና እግሩንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰበን እንደ ተጠቀለለ ወጣ፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህስ ፍቱትና ተዉት ይሂድ” አላቸው።
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
6
የዮሐንስ ወንጌል 11:38
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃብሩም ሄደ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበር፤ በላዩም ታላቅ ድንጋይ ተገጥሞበት ነበር።
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:38
7
የዮሐንስ ወንጌል 11:11
ይህንም ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፤ ከዚህም በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ላነቃው እሄዳለሁ” አላቸው።
Ṣàwárí የዮሐንስ ወንጌል 11:11
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò