1
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲሁ በጸጋው ይጸድቃሉ።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን እንዲያሳይ ነው።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “ጻድቅ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም፤ የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤ ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚሠራ አንድም የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።”
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
ሰው ሕግ ከሚያዘው ሥራ ውጭ በእምነት እንደሚጸድቅ እናምናለንና።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
Ṣàwárí ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò