1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:26
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:27
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:11
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ማንም ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:33
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ እንዳለው አስቀድሞ ተቀምጦ ወጪውን የማይቈጥር ማን ነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢያኖር፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ።
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ለምድርም ሆነ ለፍግ መቈለያ አይጠቅምም፤ ወደ ውጭም ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
Ṣàwárí የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò