1
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እንዲህም ሲል እግዚአብሔር ተናገረ፦ “በእኔና በእናንተ፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም የማደርገው፥ የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፥ ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ፥ ይህም በእኔና በምድር መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
2
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
ቀስቲቱም በደመና ስትሆን፥ አያታለሁም በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
3
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
4
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
5
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
ከዚህ በፊት የአትክልት ዓይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
7
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።”
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò