1
ኦሪት ዘፍጥረት 21:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ለሣራ መልካም በማድረግ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመላት።
Ṣe Àfiwé
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18
እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤ ተነሺ፤ ሂጂና ልጁን አንሥተሽ ዕቀፊው የእርሱንም ዘር አበዛለሁ፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ” አላት።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18
3
ኦሪት ዘፍጥረት 21:2
ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:2
4
ኦሪት ዘፍጥረት 21:6
ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:6
5
ኦሪት ዘፍጥረት 21:12
እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:12
6
ኦሪት ዘፍጥረት 21:13
የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ልጅ ስለ ሆነ ታላቅ ሕዝብ እስኪሆን ድረስ ዘሩን አበዛለሁ” አለው።
Ṣàwárí ኦሪት ዘፍጥረት 21:13
Ilé
Bíbélì
Àwon ètò
Àwon Fídíò