1
ማቴዎስ 5:15-16
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
ሰዎችም መብራት አብርተው ከእንቅብ በታች አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
موازنہ
تلاش ማቴዎስ 5:15-16
2
ማቴዎስ 5:14
“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤
تلاش ማቴዎስ 5:14
3
ማቴዎስ 5:8
ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
تلاش ማቴዎስ 5:8
4
ማቴዎስ 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።
تلاش ማቴዎስ 5:6
5
ማቴዎስ 5:44
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤
تلاش ማቴዎስ 5:44
6
ማቴዎስ 5:3
“በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
تلاش ማቴዎስ 5:3
7
ማቴዎስ 5:9
ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።
تلاش ማቴዎስ 5:9
8
ማቴዎስ 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና።
تلاش ማቴዎስ 5:4
9
ማቴዎስ 5:10
ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
تلاش ማቴዎስ 5:10
10
ማቴዎስ 5:7
ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።
تلاش ማቴዎስ 5:7
11
ማቴዎስ 5:11-12
“ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።
تلاش ማቴዎስ 5:11-12
12
ማቴዎስ 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
تلاش ማቴዎስ 5:5
13
ማቴዎስ 5:13
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም።
تلاش ማቴዎስ 5:13
14
ማቴዎስ 5:48
ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
تلاش ማቴዎስ 5:48
15
ማቴዎስ 5:37
ስለዚህ ስትነጋገሩ ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ ‘አዎን’፤ ‘አይደለም’ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ከክፉው የሚመጣ ነውና።
تلاش ማቴዎስ 5:37
16
ማቴዎስ 5:38-39
“ ‘ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት።
تلاش ማቴዎስ 5:38-39
17
ማቴዎስ 5:29-30
ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል። ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።
تلاش ማቴዎስ 5:29-30