1
ሉቃስ 4:18-19
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።”
موازنہ
تلاش ሉቃስ 4:18-19
2
ሉቃስ 4:8
ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።
تلاش ሉቃስ 4:8
3
ሉቃስ 4:4
ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ብሎ መለሰለት።
تلاش ሉቃስ 4:4
4
ሉቃስ 4:1
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ እንደ ተመለሰ፣ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፤
تلاش ሉቃስ 4:1
5
ሉቃስ 4:12
ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሏል” ብሎ መለሰለት።
تلاش ሉቃስ 4:12
6
ሉቃስ 4:13
ዲያብሎስ ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ።
تلاش ሉቃስ 4:13
7
ሉቃስ 4:5-8
ከዚያም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍታ ቦታ አውጥቶት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው፤ እንዲህም አለው፤ “የእነዚህ መንግሥታት ሥልጣንና ክብር ሁሉ ለእኔ ተሰጥቷል፤ እኔም ለምወድደው ስለምሰጥ፣ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።
تلاش ሉቃስ 4:5-8
8
ሉቃስ 4:9-12
ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “ ‘ይጠብቁህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል፤ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል።’ ” ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሏል” ብሎ መለሰለት።
تلاش ሉቃስ 4:9-12