1
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:8
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
Karşılaştır
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:8 keşfedin
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:5
ተስፋም ቅር አያሰኘንም፤ ምክንያቱም በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:5 keşfedin
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:3-4
በዚህ ብቻ ሳይሆን፥ መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ ስለምናውቅ በመከራም ጭምር እንመካለን፤ ጽናትም የተፈተነ ባሕርይን ያስገኝልናል፥ የተፈተነ ባሕርይም ተስፋን፤
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:3-4 keşfedin
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:1-2
እንግዲህ በእምነት ስለጸደቅን፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን፤ በእርሱም በኩል ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባት ችለናል፤ በእግዚአብሔርም ክብር በተስፋ እንመካለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:1-2 keşfedin
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6
ገና ደካሞች ሳለን፥ በትክክለኛው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6 keşfedin
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:9
እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን ይበልጡንም በእርሱ በኩል ከቁጣ እንድናለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:9 keşfedin
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:19
በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:19 keşfedin
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:11
ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5:11 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar