1
ኦሪት ዘፍጥረት 50:20
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው።
Karşılaştır
ኦሪት ዘፍጥረት 50:20 keşfedin
2
ኦሪት ዘፍጥረት 50:19
ነገር ግን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን አይደለሁም፤
ኦሪት ዘፍጥረት 50:19 keşfedin
3
ኦሪት ዘፍጥረት 50:21
ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” በዚህም ዐይነት በመልካም ንግግር በማጽናናት አረጋጋቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 50:21 keşfedin
4
ኦሪት ዘፍጥረት 50:17
‘ወንድሞችህ በበደሉህ ጊዜ ያደረሱብህን ጒዳት ሁሉ አትቊጠርባቸው ብሎሃል’ ብለን እንድንነግርህ አዞናል፤ ስለዚህ እኛ የአባትህ አምላክ አገልጋዮች ያደረስንብህን በደል ሁሉ ይቅር እንድትለን እንለምንሃለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።
ኦሪት ዘፍጥረት 50:17 keşfedin
5
ኦሪት ዘፍጥረት 50:24
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
ኦሪት ዘፍጥረት 50:24 keşfedin
6
ኦሪት ዘፍጥረት 50:25
እግዚአብሔር በሚጐበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐፅሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 50:25 keşfedin
7
ኦሪት ዘፍጥረት 50:26
ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፤ አስከሬኑንም በሽቶ አሽተው በማድረቅ በግብጽ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።
ኦሪት ዘፍጥረት 50:26 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar