1
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
Karşılaştır
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28 keşfedin
2
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26 keşfedin
3
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24 keşfedin
4
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30 keşfedin
5
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25 keşfedin
6
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው። “ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27 keşfedin
7
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29 keşfedin
8
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10 keşfedin
9
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32 keşfedin
10
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9 keşfedin
11
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar