1
ኦሪት ዘፍጥረት 21:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ለሣራ መልካም በማድረግ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመላት።
Karşılaştır
ኦሪት ዘፍጥረት 21:1 keşfedin
2
ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18
እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤ ተነሺ፤ ሂጂና ልጁን አንሥተሽ ዕቀፊው የእርሱንም ዘር አበዛለሁ፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ” አላት።
ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18 keşfedin
3
ኦሪት ዘፍጥረት 21:2
ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 21:2 keşfedin
4
ኦሪት ዘፍጥረት 21:6
ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።
ኦሪት ዘፍጥረት 21:6 keşfedin
5
ኦሪት ዘፍጥረት 21:12
እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 21:12 keşfedin
6
ኦሪት ዘፍጥረት 21:13
የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ልጅ ስለ ሆነ ታላቅ ሕዝብ እስኪሆን ድረስ ዘሩን አበዛለሁ” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 21:13 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar