1
ወደ ሮም ሰዎች 6:23
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።
Uporedi
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:23
2
ወደ ሮም ሰዎች 6:14
አሁን እናንተ የምትኖሩት ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆነ ኃጢአት ሊገዛችሁ አይገባም።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:14
3
ወደ ሮም ሰዎች 6:4
በጥምቀት ከእርሱ ጋር በተቀበርን ጊዜ የእርሱም ሞት ተካፋዮች ሆነናል፤ ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንኖራለን።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:4
4
ወደ ሮም ሰዎች 6:13
እንዲሁም የሰውነታችሁን ክፍሎች የዐመፅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታስገዙ፤ ነገር ግን ከሞት ተነሥታችሁ ሕያዋን እንደ ሆናችሁ በማድረግ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች ሁሉ የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አስገዙ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:13
5
ወደ ሮም ሰዎች 6:6
ኃጢአተኛው ሰውነታችን እንዲወገድና የኃጢአት ባሪያዎች መሆናችን እንዲቀር አሮጌው ሰውነታችን ከክርስቶስ ጋር መሰቀሉን እናውቃለን።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:6
6
ወደ ሮም ሰዎች 6:11
እንግዲህ እናንተ የመሞት ያኽል ከኃጢአት እንደ ተለያችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ግን ለእግዚአብሔር በሕይወት እንደምትኖሩ አስቡ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:11
7
ወደ ሮም ሰዎች 6:1-2
እንግዲህ ምን እንላለን? የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም! እኛ በሞት የመለየትን ያኽል ከኃጢአት የተለየን ሆነን ሳለ እንዴት በኃጢአት ጸንተን እንኖራለን?
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:1-2
8
ወደ ሮም ሰዎች 6:16
ለአንድ ሰው አገልጋዮች ሆናችሁ ለመታዘዝ ራሳችሁን ስታቀርቡ ለዚያ ለምትታዘዙለት ሰው አገልጋዮች መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም ለኃጢአት ብትታዘዙ ሞትን ለሚያመጣባችሁ ኃጢአት አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ብትታዘዙ ግን ጽድቅን ታገኛላችሁ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:16
9
ወደ ሮም ሰዎች 6:17-18
እናንተ አስቀድሞ የኃጢአት ባሪያዎች ነበራችሁ፤ አሁን ግን ለተቀበላችሁት ትምህርት ከልብ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥታችሁ የጽድቅ አገልጋዮች ሆናችኋል።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 6:17-18
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi