1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ በትዕግሥት የሚጸና ግን ይድናል።
Uporedi
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:13
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:33
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ሰዎች ይዘው ወደ ፍርድ ሲያቀርቡአችሁ፥ ‘ምን እንናገር ይሆን?’ በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ በዚያን ሰዓት የሚሰጣችሁን ብቻ ተናገሩ።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:11
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ጸንቶ ይኖራል።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:31
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
“ነገር ግን ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ የሰማይ መላእክትም አያውቁም፤ ወልድም አያውቅም።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:32
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
በአቅራቢያችሁ ጦርነት ሲደረግና በሩቅም የጦርነትን ወሬ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው፤ ይሁን እንጂ መጨረሻው ገና ነው።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:7
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
ስለዚህ የቤቱ ጌታ የሚመጣበትን ጊዜ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ምናልባትም ወደ ማታ፥ ወይም በእኩለ ሌሊት፥ ወይም ዶሮ ሲጮኽ፥ ወይም ጠዋት በማለዳ ይመጣ ይሆናል፤ በድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ትጉ። “ለእናንተ እንደ ነገርኳችሁ ለሌሎችም ሁሉ ትጉ! እላለሁ።”
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ጦርነት ያነሣል፤ በየስፍራው የምድር መናወጥና ራብ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ነው።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:8
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ወንጌል ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መዳረስ ይገባዋል።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:10
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ፤
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:6
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:9
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይመጣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳሳት ተአምራትና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋሉ።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:22
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
“በዚያን ጊዜ፥ ከዚያ ሁሉ መከራ በኋላ፥ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ በሰማይ ያሉ ኀይሎችም ይናወጣሉ።
Istraži የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi