1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ። ራሱን ዘንበል አድርጎም ነፍሱን ሰጠ።
Uporedi
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:30
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ።
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:28
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በሄዱ ጊዜ ግን፥ እርሱ ቀደም ብሎ እንደ ሞተ አይተው፥ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም በሌላው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:17
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት።
Istraži የዮሐንስ ወንጌል 19:2
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi