Logo yeApp yeBhaibheri
Mucherechedzo Wekutsvaka

ዘካርያስ 13

13
ከኀጢአት መንጻት
1“በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኀጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
2“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ። 3ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባትና እናቱ፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ሐሰት ተናግረሃልና ሞት ይገባሃል’ ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።
4“በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው የትንቢት ራእይ ያፍራል፤ ለማታለልም የነቢያትን ጠጕራም ልብስ አይለብስም። 5እርሱም፣ ‘እኔ ገበሬ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ#13፥5 ወይም ዐራሽ፤ በወጣትነቴ የተሸጥሁ ሰው ጀምሮ ኑሮዬ የተመሠረተውም በዕርሻ ላይ ነው’ ይላል። 6አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ#13፥6 በእጆችህ መኻል ያሉ ቍስሎች የሚሉ አሉ። ላይ ያለው ቍስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።”
እረኛው ተመታ፤ በጎቹ ተበተኑ
7የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣
በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ!
እረኛውን ምታ፣
በጎቹም ይበተናሉ፤
እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”
8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣
ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤
አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤
9ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤
እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤
እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤
እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤
እኔም እመልስላቸዋለሁ፤
እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤
እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

Zvasarudzwa nguva ino

ዘካርያስ 13: NASV

Sarudza vhesi

Sarudza zvinyorwa izvi

Yenzanisa

Pakurirana nevamwe

None

Unoda kuti zviratidziro zvako zvichengetedzwe pamidziyo yako yose? Nyoresa kana kuti pinda