1
የማርቆስ ወንጌል 5:34
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እርሱም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሺ፤” አላት።
Compară
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:34
2
የማርቆስ ወንጌል 5:25-26
ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች። ከሐኪም ወደ ሐኪም በመሄድ ብዙ ተሠቃይታና ገንዘብዋንም ሁሉ ጨርሳ ነበር። ነገር ግን እየባሰባት ሄደ እንጂ ምንም አልተሻላትም።
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:25-26
3
የማርቆስ ወንጌል 5:29
የሚፈሰው ደምዋም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሕመምዋም እንደ ዳነች በሰውነትዋ ተሰማት።
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:29
4
የማርቆስ ወንጌል 5:41
የልጅትዋንም እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ትርጒሙም “አንቺ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ፤” ማለት ነው።
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:41
5
የማርቆስ ወንጌል 5:35-36
ኢየሱስ ገና ይህን በመናገር ላይ ሳለ ከምኲራብ አለቃው ቤት የመጡ ሰዎች የምኲራብ አለቃውን፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ ስለምን መምህሩን ታደክመዋለህ?” አሉት። ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ የምኲራቡን አለቃ፦ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ!” አለው።
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:35-36
6
የማርቆስ ወንጌል 5:8-9
ይህንንም ያለበት ምክንያት፥ “አንተ ርኩስ መንፈስ ከዚህ ሰው ውጣ!” ብሎ አዞት ስለ ነበር ነው። ኢየሱስም “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም “ብዙዎች ስለ ሆንን ስሜ ሌጌዎን ነው፤” ሲል መለሰለት።
Explorează የማርቆስ ወንጌል 5:8-9
Acasă
Biblia
Planuri
Videoclipuri