1
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል። ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ።
Compare
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ወደ ሮም ሰዎች 3:22
ስለዚህ እግዚአብሔር ምንም ልዩነት ሳያደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ጽድቅን ይሰጣል።
ወደ ሮም ሰዎች 3:22ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው። በአሁኑም ዘመን እግዚአብሔር ራሱ ጻድቅ መሆኑን የሚያሳየው በኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ በማጽደቅ ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ወደ ሮም ሰዎች 3:20
ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 3:20ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ “አንድ እንኳ ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድ እንኳን የለም፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ አንድም የለም። ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነት ሆነው ተሳስተዋል። ደግ ሥራ የሚሠራ አንድ ሰው እንኳ የለም።
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ወደ ሮም ሰዎች 3:28
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን የሚያጸድቀው፥ ሰው የሕግን ሥራ በመፈጸሙ ሳይሆን በእምነት መሆኑን እንገነዘባለን።
ወደ ሮም ሰዎች 3:28ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ወደ ሮም ሰዎች 3:4
ከቶ አያስቀርም! “ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤ ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 3:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ