1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ በትዕግሥት የሚጸና ግን ይድናል።
Compare
የማርቆስ ወንጌል 13:13ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ሰዎች ይዘው ወደ ፍርድ ሲያቀርቡአችሁ፥ ‘ምን እንናገር ይሆን?’ በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ በዚያን ሰዓት የሚሰጣችሁን ብቻ ተናገሩ።
የማርቆስ ወንጌል 13:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ጸንቶ ይኖራል።
የማርቆስ ወንጌል 13:31ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
“ነገር ግን ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ የሰማይ መላእክትም አያውቁም፤ ወልድም አያውቅም።
የማርቆስ ወንጌል 13:32ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
በአቅራቢያችሁ ጦርነት ሲደረግና በሩቅም የጦርነትን ወሬ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው፤ ይሁን እንጂ መጨረሻው ገና ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
ስለዚህ የቤቱ ጌታ የሚመጣበትን ጊዜ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ምናልባትም ወደ ማታ፥ ወይም በእኩለ ሌሊት፥ ወይም ዶሮ ሲጮኽ፥ ወይም ጠዋት በማለዳ ይመጣ ይሆናል፤ በድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ትጉ። “ለእናንተ እንደ ነገርኳችሁ ለሌሎችም ሁሉ ትጉ! እላለሁ።”
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ጦርነት ያነሣል፤ በየስፍራው የምድር መናወጥና ራብ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:8ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ወንጌል ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መዳረስ ይገባዋል።
የማርቆስ ወንጌል 13:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ፤
የማርቆስ ወንጌል 13:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:9ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይመጣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳሳት ተአምራትና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:22ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
“በዚያን ጊዜ፥ ከዚያ ሁሉ መከራ በኋላ፥ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ በሰማይ ያሉ ኀይሎችም ይናወጣሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ