1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ። ራሱን ዘንበል አድርጎም ነፍሱን ሰጠ።
Compare
የዮሐንስ ወንጌል 19:30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:28ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በሄዱ ጊዜ ግን፥ እርሱ ቀደም ብሎ እንደ ሞተ አይተው፥ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም በሌላው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤
የዮሐንስ ወንጌል 19:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት።
የዮሐንስ ወንጌል 19:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ