1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
Compare
የዮሐንስ ወንጌል 15:5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:13ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:8ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤
የዮሐንስ ወንጌል 15:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:19ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ