1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።
Compare
የዮሐንስ ወንጌል 14:27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።
የዮሐንስ ወንጌል 14:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤
የዮሐንስ ወንጌል 14:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኳችሁንም ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 14:26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
“እኔን የሚወደኝ ትእዛዜን የሚቀበልና በሥራ ላይ የሚያውለው ነው፤ እኔንም የሚወደኝን አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 14:21ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔ አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል። ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ ምክንያት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ፤
የዮሐንስ ወንጌል 14:15ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ አለበለዚያ ግን ‘የምትኖሩበትን ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ’ ባልኳችሁ ነበር።
የዮሐንስ ወንጌል 14:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄ ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ እኔ ባለሁበት እንድትኖሩ እንደገና መጥቼ እወስዳችኋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስ “ጌታ ሆይ! ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ ታዲያ፥ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 14:5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ