1
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
Compare
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24
ከጌታ የተቀበልኩትና ለእናንተም ያስተላለፍኩላችሁ ትምህርት ይህ ነው፤ ጌታ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ኅብስት አነሣ፤ የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29
ስለዚህ ማንም ሰው ይህን ኅብስት ከመብላቱና ይህንንም ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት ራሱን መመርመር አለበት። ማንም ሰው የጌታ ሥጋ ምን መሆኑን ለይቶ ሳያውቅ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታን ጽዋ ቢጠጣ በራሱ ላይ ፍርድን ያመጣል።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27
ማንም ሰው ያልተገባው ሆኖ ሳለ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታንም ጽዋ ቢጠጣ የጌታን ሥጋና ደም በማቃለሉ ይጠየቅበታል።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ