1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።
तुलना
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹም ቀኑበት፥ አባቱ ግን ነገሩን ጠብቆ አኖረው።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም አላቸው፦ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፥ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ፥ እንግደለውና በአንዱ ጉድጓድ ውስጥ እንጣለው፦ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፥ የሕልሞቹን መጨረሻ እናያለን።”
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ ይኸው መጣ።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
“ደም አታፍስሱ፥ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጉድጓድ ጣሉት፥ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት” አላቸው። እንዲህም ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው።
अन्वेषण गर्नुहोस् ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
होम
बाइबल
भक्त्ति पाठहरू
भिडियोहरू