1
የማቴዎስ ወንጌል 23:11
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።
နှိုင်းယှဉ်
የማቴዎስ ወንጌል 23:11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የማቴዎስ ወንጌል 23:12
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
የማቴዎስ ወንጌል 23:12ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የማቴዎስ ወንጌል 23:23
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
የማቴዎስ ወንጌል 23:23ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የማቴዎስ ወንጌል 23:25
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።
የማቴዎስ ወንጌል 23:25ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የማቴዎስ ወንጌል 23:37
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
የማቴዎስ ወንጌል 23:37ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የማቴዎስ ወንጌል 23:28
እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል።
የማቴዎስ ወንጌል 23:28ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ