1
የማቴዎስ ወንጌል 27:46
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።
နှိုင်းယှဉ်
የማቴዎስ ወንጌል 27:46ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የማቴዎስ ወንጌል 27:51-52
እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
የማቴዎስ ወንጌል 27:51-52ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የማቴዎስ ወንጌል 27:50
ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:50ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የማቴዎስ ወንጌል 27:54
የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:54ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የማቴዎስ ወንጌል 27:45
ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:45ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23
ጲላጦስ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ። ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ