1
የማቴዎስ ወንጌል 18:20
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት ስፍራ እኔ በመካከላቸው እገኛለሁ።”
နှိုင်းယှဉ်
የማቴዎስ ወንጌል 18:20ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የማቴዎስ ወንጌል 18:19
ደግሞም እላችኋለሁ፤ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ላይ ማናቸውንም ነገር ለመለመን ተስማምተው ቢጸልዩ፥ በሰማይ ያለው አባቴ ይፈጽምላቸዋል።
የማቴዎስ ወንጌል 18:19ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የማቴዎስ ወንጌል 18:2-3
ኢየሱስም አንድ ሕፃን ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ፤ እንዲህም አለ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፦ ካልተለወጣችሁና እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ከቶ ወደ መንግሥተ ሰማይ አትገቡም።
የማቴዎስ ወንጌል 18:2-3ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የማቴዎስ ወንጌል 18:4
እንደዚህ ሕፃን ራሱን ዝቅ የሚያደርግ በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይሆናል።
የማቴዎስ ወንጌል 18:4ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የማቴዎስ ወንጌል 18:5
እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል።
የማቴዎስ ወንጌል 18:5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የማቴዎስ ወንጌል 18:18
“በእውነት እላችኋለሁ፤ በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም በሰማይ የተፈታ ይሆናል።
የማቴዎስ ወንጌል 18:18ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
የማቴዎስ ወንጌል 18:35
“እንግዲህ እናንተም እያንዳንዳችሁ ወንድማችሁን ከልብ ይቅር ባትሉ በሰማይ ያለው አባቴም እንዲሁ ያደርግባችኋል።”
የማቴዎስ ወንጌል 18:35ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
8
የማቴዎስ ወንጌል 18:6
“ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢጣልና ቢሰጥም ይሻለዋል።”
የማቴዎስ ወንጌል 18:6ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
9
የማቴዎስ ወንጌል 18:12
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እስቲ ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን አንዱን ለመፈለግ አይሄድምን?
የማቴዎስ ወንጌል 18:12ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ